የሆድ_ድርቀት

#የሆድ_ድርቅት

ከሚከተሉት ምልክቶች ውስጥ ሁለቱ ካጋጠሙዎት የሆድ ድርቀት ሊኖርብዎት ይችላል፡

• በሳምንት ከሶስት ጊዜ ያነሰ ሽንት ቤት መሄድ🚽

• ደረቅ ሰገራ ማሳለፍ

• ሽንት ቤት በሚጠቀሙበት ወቅት ውጥረት ወይም የማስማጥ እና ህመም ካለዎ

• ሽንት ቤት ቢጠቀሙም እንኳን ሆዶ የመሞላት ወይም ያለመቅለል ስሜት

#የተለመዱ የሆድ ድርቀት መንስኤዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ :­

•በምግብ ውስጥ የፋይበር መጠን ማነስ፣ በተለይም ስጋ፣ ወተት ወይም አይብ አብዛኛውን ጊዜ ሚመገቡ ከሆነ

•የሰውነት ድርቀት (ውሃ በበቂ ሁኔታ ባለመጠጣት)

•የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ

•ሽንት ቤት መሄድን ማዘግየት

•አንዳንድ ለጨጓራ የሚውሰዱ መድኃኒቶች፣ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች፣ ለፓርኪንሰን ሕክምናዎች የሚውሉ መድሃኒቶች

•እርግዝና

•የዕድሜ መግፋት (60 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች)👨🏿‍🦳

#የሚከተሉት የጤና ችግሮች የሆድ ድርቀት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡−

•እንደ ስትሮክ፣ ፓርኪንሰንስ ፣ የአንጀት ወይም ፊንጢጣ ላይ ያሉ እክሎች፣የስኳር ህመም፣ከመጠን በላይ ወይም አላግባብ ጥቅም ላይ የሚውሉ መድሃኒቶች፣የታይሮይድ ሆርሞን ማነስ ወዘተ…

#የሚከተሉትን ካስተዋሉ በፍጥነት ሀኪም ሊያዮት የገባል፡-

•ከፊንጢጣ ደም መፍሰስ

•ሰገራ ውስጥ ደም

•የማያቋርጥ የሆድ ህመም

•ማስታወክ

•ትኩሳት

•ድንገት ወይም ያልተጠበቀ ክብደት መቀነስ

#ህክምናና መከላከያ መንገዶች

• አመጋገብን መቀየር እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን መጠን መጨመር የሆድ ድርቀትን ለማከም እና ለመከላከል ቀላሉ እና ፈጣኑ መንገዶች ናቸው።

እንዲሁም የሚከተሉትን ዘዴዎች መሞከር ይችላሉ፡-

• በየቀኑ ከ 1.5 እስከ 2 ሊትር ውሃ መጠጣት

• አልኮል እና ካፌይን ያላቸውን መጠጦች ከመጠቀምን ይቆጠቡ

• በአመጋገብዎ ውስጥ በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ያካትቱ፣ ለምሳሌ ኦርጋኒክ የሆኑ ፍራፍሬ እና አትክልት፣ ባቄላ፣ ፕሪም፣እንጆሪ ፣አቮካዶ፣ፖም፣ሙዝ፣ካሮት፣ብሮኮሊ፣አጃ፣ስኳር ድንች፣ራስቤሪ፣ቲማቲም፣ምስር፣ለውዝ፣አተር፣ ትርንጎ ወዘተ (ምን ቀረ እንዳትሉኝ ሃሃ)በየቀኑ የሚወስዱት የፋይበር መጠን ከ20 እስከ 35 ግራም መሆን አለበት

• እንደ ስጋ፣ ወተት፣ አይብ እና ፕሮሰስድ ምግቦችን ይቀንሱ

• በቀን መጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማደርግ ቢያንስ 30 ደቂቃ ይስሩ በእግር መሄድ፣ መዋኘት ወይም ብስክሌት መንዳት

• ሽንት ቤት የመሄድ ፍላጎት ከተሰማዎት አይዘገዩ ፤ በቆዩ ቁጥር የሰገራ መድረቅ ያመጣል

ከላይ የተመለከትናቸውን መንገዳች በመጠቅም የሆድ ድርቀትን መከላከል ይችላል ሆኖም ግን አንዳንዴ ችግሩ ከበረታ ሀኪሞ አጋዥ መድኃኒቶችን የሚይዝበት አግባብ ይኖራል።

ዳ/ር ግሩም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *