ህልም ምንድን ነው? መነሻውስ ምን ይሆን? ለምን ያለፈቃዳችን እናልማለን? ለማለም በፈለግን ጊዜ ለምን አናገኘውም? ህልማችንን እንዴት መቆጣጠር እንችላለን? ይህንን እና መሰል ጥያቄዎች የሰው ልጆችን ከጥንት ጀምሮ በብዙ ሲያነጋግሩ እና ሲያፈላስፉ ኖረዋል። ቢሆንም ግን ከነገሱ ውስብስብነት የተነሳ ይሄ ነው የሚባል ተጨባጭ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ አልተቻለም። ቢሆንም ግን የተለያዩ ትውፊቶች እና ሀይማኖቶች ስለ ህልም ምንነት እና አተረጓጎም የየራሳቸው የሆነ እይታ አላቸው።
ለምሳሌ እንደ ሂንዱይዝም እይታ በህልም ወቅት ነፍሳቸን ከሰውነታችን ወጥታ ስትንቀሳቀስ የሚያጋጥማትን ነገር ነው የምናልመው ይላሉ። ከዚህ በተለየ መልኩ የአብርሀማዊ እምነቶች የሆኑት ይሁዲ፣ እስልምና እና ክርስትና ደግሞ አምላክ ለሰው ልጆች መልዕክትን ለማስተላለፍ የሚጠቀምበት መንገድ እንደሆነ ያስተምራሉ።
አጥኚዎች እንደሚናገሩት ሁላችንም በየቀኑ ህልም እናልማለን። አንዳንዶቹ ከነቁ በኋላም ህልማቸውን ማስታወስ ሲችሉ ሌሎቹ ደግሞ የተወሰነ ያህል ወይም ሙሉ በሙሉ አያስታውሱም። እናንተም ይህንን ቪዲዮ ለማየት ከመረጣችሁ ከዚህ በፊት ልዩ የሆነ ህልም አይታችሁ የምታውቁ ወይም ስለ ህልም ምንነት እና ትርጉሙ እንዲሁም ህልማችሁ ከማንነታችሁ ጋር ያለውን ግንኙነት የማወቅ ጥልቅ ፍላጎት አላችሁ ማለት ነው። ሳይሳዊ ጥናቶች እንድሚያመላክቱት ከሆነ ህልሞች ከውስጠኛው ማንነታችን ጋር የጠለቀ ግንኙነት ስላላቸው ስለ እኛ ብዙ የሚናገሩት ነገር አለ። የህልሞች ትርጉም ሁልጊዜም ቀጥተኛ እና ግልጽ ባይሆንም ህልማችሁ የስሜታችሁ እና የሀሳባችሁ መግለጫ ነው። በተጨማሪም ስለ ማንነታችሁ እና ስለ ጤንነታችሁ ሳይቀር ከህልማችሁ ብዙ መረዳት ትችላላችሁ። ስትተኙ አምሯችሁ ምንድን ነው ሊነግራችሁ የፈለገው ነገር?
1. ምን ያህል አዲስ ነገር ፈጣሪ መሆናችሁን
ማቆሚያ የሌለው በሚመስል መልኩ ቀንም በሌሊት ሌሊትም በቀን እየተተካካ ጊዜያት ይሄዳሉ። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ቀን ላይም ሆነው ሳይተኙ ፣ አይናቸውንም መጨፈን ሳይጠበቅባቸው እንዲሁ ያልማሉ። እነዚህ አይነት ሰዎች በቶሎ መተኛትም ሆነ በቶሎ መነሳት ይችላሉ። ስለዚህ እንቅልፍ እስኪወስዳቸው ወይም ከእንቅልፋቸው እስኪነቁ ሰፊ ሰዓት አይወስድባቸውም። ብዙ የሚያስቡ፣ አርቀው የሚያዩ፣ ነገሮችን በተለየ እይታ የሚያዩ፣ በተለይም የጥብብ ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ከሌሎች በተለየ መልኩ ግልጽ ህልሞችን ያያሉ። በቤት ውስጥ ሆነው፣ ወይም ስራ ቦታ ላይ ሆነው ሲሰሩ ሳይሆን የሚታያቸው አዳዲስ እና የማይታወቁ ነገሮችን ሲሞክሩ፣ ሌላ አለማት ላይ ሲዝናኑ አይነት ነገር ነው የሚያልሙት።
2. የስራ ባህሪያችሁን
ሁሌም ስራ ላይ የተጠመዳችሁ እና በጣም ቢዚ ሰዎች ናችሁ ወይስ ከራሳችሁ ጋር የምታሳልፉበት፣ የምታርፉበት እና የምታስቡበት የተለየ ጊዜ አላችሁ? በጣም ስትለፉ የምትውሉ እና የየለት ፕሮግራማችሁ የተጣበበ ከሆነ ህልማችሁ አስጨናቂ እና አድካሚ ይሆንባችኋል። ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ እረፍት የምትወስዱ እና ከመጠን በላይ በስራ ራሳችሁን የማታጨናንቁ ከሆነ ቀለል ያለ አስቸጋሪ ህልሞችን በማየት አትቸገሩም።
3. የልብ ህመም ተጋላጭነትን
በተደጋጋሚ ቅዠት የሚያጋጥማቸው ሰዎች ምናልባትም የልብ ችግር ወይም ደረት አካባቢ ያለ የጤና አክል ሊኖርባቸው ይችላል። ጥናቶች እንደሚያመላክቱት የልብ ህመም ያለባቸው ሰዎች ከሌሎች ሰዎች በተለየ የሌሊት ቅዠት በ 3 እጥፍ ሲያጋጥማቸው፣ የደረት አካባቢ ህመም ያለባቸው ሰዎች ደግሞ 7 እጥፍ ለቅዠት ተጋላጭ ናቸው። ለዚህም ምክኒያቱ የልብ
ችግር ያለባቸው ሰዎች የአተነፋፈስ ችግር በቀላሉ ስለሚያጋጥማቸው ይሆናል። ይህም ለአዕምሯቸው የሚደርሰውን የኦክሲጅን መጠን በእጅጉ ይቀንሰዋል።
4. ችግር ፈቺዎች መሆናችሁን
ተኝታችሁ እያለ በህልም ላይ እንደሆናችሁ ይሰማችኋል? ስታልሙ ታውቁታላችሁ? መልሳችሁ አዎ ከሆነ እናንተ ብርሀናማ እና ግልጽ የሆነ ህልምን የምታዩ ሰዎች ናችሁ ማለት ነው። ጥናቶች እንድሚያሳዩት ከሆነ ብርሀናማ እና ግልጽ የሆነ ህልም የሚያዩ ሰዎች ችግሮችን በእርጋታ እና በጥበብ የምፍታት ትልቅ አቅም አላቸው። ህልም እያለሙ እንደሆነ የሚያውቁ ሰዎች ነገርን በጥልቀት የሚመረምሩ እና አስተዋዮች ናቸው። ይህም የተለያዩ የህይወት ፈተናዎች እና ውጣ ውረዶች በሚያጋጥማቸው ጊዜ የተሻለ ውሳኔ መወሰን እንዲችሉ ይረዳቸዋል።
5. የፖለቲካ እይታዎቻችሁን እና ሀሳባችሁን
የፖለቲካ እይታዎች አብዛኛውን ጊዜ የሰውን ማንነት እና አስተሳሰብ ያሳያሉ። የምታምኑት የፖለቲካ እሳቤ ስለ አለም ያላችሁ እይታ ላይ ትልቅ ሚና አለው። ወግ አጥባቂ የሚባል አይነት አስተሳሰብ የሚያራምዱ ሰዎች የሚያልሟቸው ህልሞች ተግባራዊ የሆኑ ህልሞችን ሲያዩ ፤ ከዚህ በተለየ መልኩ ደግሞ ነጻ አስተሳሰብን የሚያራምዱ ሰዎች ወጣ ያሉ እና ግራ የሚያጋቡ ህልሞችን ያልማሉ።
6. በቂ እንቅልፍ አለማግ ኘታችሁን ወይም ከእንቅልፍ ጋር የተያያዘ ችግር እንዳለባችሁ
ብዙ ጊዜ በህልማችሁ ስትሰጥሙ ወይም ታፍናችሁ መተንፈስ አቅቷችሁ አይነት ህልሞች ታያላችሁ ? መልሳችሁ አዎ ከሆነ ምናልባትም ከእንቅልፍ ጋር የተያያዘ የጤና ችግር እንዳለባችሁ ሰውነታችሁ ሊነግራችሁ እየሞከረ ነው። ስለዚህ ለነገሩ ትኩረት ሰጥታችሁ መፍትሄ ፈልጉለት። ምናልባት sleep apnea ለሚባል ህመም ተጋልጣችሁ ይሆናል። ይሄ ህመም ሰዎች በእንቅልፍ ላይ እያሉ ለተወሰነ ጊዜ ያህል መተንፈስን እንዳይችሉ የሚያደርግ ነው። በዚህ ህመም የተጠቁ እና አስፈላጊዉን የህክምና ክትትል ያደረጉ ህሙማን 91% ጤናቸው እንደተስተካከለ ጥናቶች ያሳያሉ።
7. ትኩረት ያልሰጣችሁት የስሜት ችግር እንዳለ
ህልሞች በዋናነት ሰውነታችን የሚያጋጥሙትን ነገሮች የሚገልጽበት መንገዶች ናቸው። በየጊዜው ተመሳሳይ የሆነ ህልም የምታዩ ከሆነ የሆነ ያስቸገራችሁ እና ልትፈቱት ያልቻላችሁ ከስሜት ጋር የተያያዘ ችግር እንዳለ አመላካች ነው። እንደዚህ አይነት ችግሮችን ለመፍታት ህልማችሁ ምን እንዲሰማችሁ እንዳደረገ አስቡ። የትኛው በእውነተኛ ህይወታችሁ ያለ ነገር ነው በህልማችሁም እንደዛ እንዲሰማችሁ እያደረገ ያለው?
8. የምትወስዱትን የመድሀኒት አይነት
በጣም ብዙ አይነት መድሀኒቶች ልክ እንደ anti-depressants, anti-biotics, satins እና anti-histamines ከመጥፎ ህልሞች እና ቅዠቶች ጋር አብረው ይነሳሉ። Beta Blockers የተባሉ ለደም ግፊት የሚታዘዙ መዳኒቶችም አጅግ አስቸጋሪ እና የሚረብሹ ህልሞችን እንደሚያስከትሉ ይታመናል። እነዚህ መድሀኒቶች በደንብ ቧንቧ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ቢጠቅሙም አንዳንድ ጊዜ ግን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአዕምሮ ሴሎች ውስጥ ያሉ ኬሚካሎችን እንደሚለውጡ በጥናት ተረጋግጧል። ይህም በእንቅልፍ ሰዓት ላይ ቅዠት እንዲያጋጥም ምክኒያት ይሆናል።
9. ከማን ጋር በደንብ እንደምትቀራረቡ
ህልሞቻችሁ የውስጥ ስሜታችሁን ጋር የጠበቀ ግንኙነት ስላላቸው ውስጣችሁን የመግለጽ ትልቅ አቅም አላቸው። በህይወታችሁ ውስጥ በጣም የምትቀርቧቸውን ሰዎች በህልማችሁ የማየት እድላችሁ በጣም ሰፊ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። ለምሳሌ አብዛኛውን ጊዜ ከአባታችሁ ይልቅ እናታችሁ የምታዩ ከሆነ ከአባታችሁ ይልቅ ከእናታችሁ ጋር እጅግ በጣም እንደምትቀራረቡ መናገር ይቻላል።
10. የነርቭ ወይም የአዕምር ህመም ተጋላጭነትን
በተደጋጋሚ በህልማችሁ ውስጥ frail trash ምናልባትም disorder ህመም ተጋልጣችሁ ሊሆን ይችላል። አጥኚዎች እንደሚናገሩት ከሆነ ይሄ ነገር የሚከሰተው በአዕምሯችሁ ውስጥ በህልም ሰዓት ላይ ከመንፈራገጥ እና ሌላ ነገሮችን ከማድረግ የሚጠብቃችሁ ክፍል ሲጎዳ ነው። ይህም ተኝቶ እያለመ ያለው ሰው በመንገድ ላይ ሰዎች ሲያግቱት ወይም ሲደበድቡት እንዲያይ ያደርገዋል። ከዚህም የተነሳ ያ ሰው አልጋ ላይ ሆኖ ህልም ላይ እንዳለ ይንፈራገጣል፣ ትራሶችን ይመታል ምናልባትም አጠገቡ ሰው ካለ ያን ሰው ሊመታ ይችላል። እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ሲደጋገም የአልዛይመር እና የፓርኪንሰንስ ህመም መኖሩን ያሳያል። ምናልባትም ህመሙ ከመከሰቱ ከ10 አመታት በፊት እነዚህ ምልክቶች ቀድመው ሊታዩ ይችላሉ።
11. Migraine /የራስ መርዘን/ ሊነሳባችሁ መሆኑን
የማይግሬይን ከፍተኛ ራስ ምታት አብዛኛውን ጊዜ የሚነሳው በምሽት ወይም ሌሊት ላይ ነው። እንደ ጥናቶች ውጤት ከሆነ ደግሞ የማይግሬይን ህመም በሌሊት ላይ በሚነሳበት ሰዓት አስፈሪ እና የንዴት ስሜት የቀላቀለባቸውን ህልሞች ይዞ ይከሰታል። እነዚህን አስጨናቂ ህልሞችን ማይሬይን አይደለም የሚያመጣው። ይልቁንም ተኝታችሁ እያለ እነዚህን አይነት ህልሞች በምታልሙበት ጊዜ አዕምሯችሁ ወስጥ ያሉ ሴሎች እና ነርቫችሁ በተለይም የተባለው occipital ነርቭ ላይ ጫና ያሳድራል። ይሄም የማይግሬይን ራስ ምታትን ያነሳሳል።
12. ለሴቶች፣ የሴቶች ፔሬድ ወይም የወር አበባ ቀን እየደረሰ መሆኑን
አንዳንድ ሴቶች ከወር አበባቸው መምጫ ቀን ቀደም ብሎ አስቸጋሪ ህልም ያልማሉ። ይህም የሚያሳየው የሆርሞን መጠን ህልሞች ላይ የሆነ ያህል ተፅዕኖ እንዳለው ነው። ሴቶች ከወር አበባ ጊዜያት ቀደም ብሎ የሆርሞን መጠን መዛባት ያጋጥማቸዋል። ይህም ለአስቸጋሪ እንቅልፍ እና ለቅዠት መንስኤ ይሆናል። ለዚህም ምክኒያቱ የወር አበባ ከምጣቱ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ REM እንቅልፍ ይቀንሳል። እንደሚታወቀው ህልም ደግሞ የሚከሰተው በ REM እንቅልፍ ወቅት ነው። ስለዚህ አንዲት ሴት የወር አበባዋ በሚደርስበት ጊዜ ከሌሎች ጊዜያት በተለየ ህልም እያለመች ሳይሆን ከነቃች በኋላ የምታልመውን ህልሞች እያስታወሰች ነው። ይህም ከወር አበባ ጋር ተያይዞ በሚመጣው የህመም እና ምቾት የማጣት ስሜት የተነሳ ነው።
አሁንም ቢሆን ስለህልም እጅግ በጣም ብዙ ሳይንስ ያልደረሰባቸው ነገሮች ቢኖሩም ሳይንቲስቶች አሁንም በመመራመር እና ህልሞች ላይ ጥናቶችን በማድረግ ላይ ናቸው። ህልሞች በዕለት ተዕለት ህይወታችን ላይ ያላቸው ተፅዕኖ ሊካድ የማይችል ነው። በርግጥ ህልሞች ከሰው ሰው ይለያያሉ። ትርጉማቸውም እንደየሰው ሀሳብ የተለያየ ነው ። ስለዚህ ሰዎች ለህልሞች
የሚሰጡት ትርጓሜ ይለያያል። ቢሆንም ግን ህልማችሁን ማወቅ፣ አንዱ ህልም ከሌላው ህልም ያለውን ተመሳሳይነት እና ልዩነት ማወቅ እንዲሁም ህልሞች በህይወታችሁ ላይ ያላቸውን ተፅዕኖ ማወቅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ምናልባትም ሰውነታችሁ በህልማችሁ በኩል ለናንተ ሊነግራችሁ የፈለገው ነገር አለ ማለት ነው።
ምን ታስባላችሁ? የተዘረዘሩት ነገሮች ከናንተ ጋር ይሄዳሉ? ሀሳባችሁን እና አስተያየታችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን።