ስለኩላሊት ካንሰር

(Renal cell cancer)

በጥቂቱ እነሆ:-

መግቢያ፦ በአሁኑ ጊዜ የኩላሊት ካንሰር(incidence) እየጨመረ ቢመጣም ገዳይነቱ ግን እየቀነሰ መምጣቱን ጥናቶች ያሳያሉ። ይህም ሊሆን የቻለው ህብረተሰቡ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ምርመራ የማድረግ ልምድ ማዳበሩና በቀላል ምርመራ ማወቅ በመቻሉ በጊዜ ህክምናው ስለሚሰጥ ነው።

ለኩላሊት ካንሰር አጋላጭ ነገሮች(risk factors)

1) እድሜ መጨመር(ageing)

በተለይ 60 እና 70ዎቹ የዕድሜ ክልል ላይ የመከሰት ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

2) ወንድ መሆን( male gender)

ወንዶች ላይ የመከሰት ዕድሉ ከሴቶች የበለጠ ነው(M:F=~2:1)።

3) በዘረመል(genetic)

በዘር የመከሰት ዕድሉ በሁለት እጥፍ(2x) የሚደርስ ነው። በዘረመል የሚመጣው ካንሰር በወጣትነት የዕድሜ ክልልና በሁለቱም ኩላሊቶች ላይ ሊከሰት ይችላል።

4) ሲጋራ ማጨስ(smoking)

5) ውፍረት(obesity)

6) የደም ግፊት (hypertension)

7) በደም ዕጥበት የሚታከም የቆየ ኩላሊት ድክመት (chronic renal failure on dialysis)

የኩላሊት ካንሰር አይነቶች(histology)

ዋና ዋናዎቹ የኩላሊት ካንሰር አይነቶች:-

1) Clear cell Renal cell cancer

አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው(~75%) የኩላሊት ካንሰር አይነት ነው።

2) Papillary Renal cell cancer

ከ10-15% የሚከሰት የኩላሊት ካንሰር አይነት ነው።

3) Chromophobe renal cell cancer

እስከ 5% የሚከሰት የኩላሊት ካንሰር አይነት ነው።

4) Cortical duct carcinoma

በአብዛኛው ታችኛው የዕድሜ ክልል ላይ የሚከሰት የኩላሊት ካንሰር ሲሆን ብዙውን ጊዜ አይከሰትም(rare)።

5) Renal medullary carcinoma

በጣም ሊከሰት የማይችል(very rare) ነገር ግን በጣም ገዳይ የኩላሊት ካንሰር አይነት ነው። በልዩነት የሲክል ሴል በሽተኞች(sickle cell disease) ላይ ይከሰታል።

እነዚህ የካንሰር አይነቶች በባሪያቸው ቅደም ተከተል ሲቀመጡ

*Papillary RCC(የተሻለው)–>Chromophobe RCC–>Clear cell RCC–> Collecting duct Ca–>Renal medullary ca(መጥፎው)

የኩላሊት ካንሰር ምልክቶች

50%ቱ ለሌላ ህክምና በሚደረግ የአልትራሳውንድ/ሲቲ ስካን ምርመራ ወቅት በአጋጣሚ የሚታወቅ/የሚገኝ(incidental) ነው። ይህም ማለት አብዛኛው የኩላሊት ካንሰር ምንም ምልክት ላያሳይ ይችላል።

የሽንጥ ህመም(flank pain)

የሽንጥ ዕብጠት(flank mass)

ደም የቀላቀለ ሽንት(haematuria)

እነዚህ ሦስቱ ምልክቶች ከታዩ የካንሰር ደረጃው ከፍ ያለ መሆኑንም ያመላክታሉ።

ሌሎች ምልክቶች

ክብደት መቀነስ

የደም ግፊት(hypertension)

በደም ውስጥ የካልሽየም መጠን መጨመር(hypercalcemia)

የደም ማነስ(anemia) ወይም የደም መብዛት(polycythemia)

የጉበት ችግር መከሰት(Stauffer’s syndrome)

የኩላሊት ካንሰር መኖሩ በሚታወቅበት ጊዜ እስከ 20% ድረስ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ተሰራጭቶ ሊገኝ ይችላል። ይህም በደም ዝውውር ወይም በሊፍፋቲክ(hematogeneous or lymphatic) ሊሰራጭ ይችላል። በደም ዝውውር ወደ ሳንባ፣ አጥንት፣ ጉበትና አንጎል ሊሰራጭ ይችላል።

የምርመራ መንገዶች

1) አልትራሳውንድ(ultrasound)

ካንሰር መኖር አለመኖሩን በአልትራሳውንድ (በእርግጠኝነት ባይሆንም) ማወቅ ይቻላል።

2) ሲቲ ስካን(CT scan): ከአልትራሳውንድ በተሻለ የካንሰሩን መኖርና የካንሰሩን ደረጃ(stage) ለማወቅ ይጠቅማል።

3) MRI: በCT scan ማወቅ ካልቸቻለ ወይም CT scan ማንሳት የማይቻልባቸው ምክንያቾች ሲኖሩ ይታዘዛል።

የኩላሊት ካንሰር ደረጃዎች(staging)

እንደማንኛውም የካንሰር አይነት አራት ደረጃዎች(stage 1-stage 4) ሲኖሩት ደረጃው በጨመረ ቁጥር በካንሰር የመኖር(cancer specific survival)ዕድሜን ይቀንሳል:: ይህም ማለት በደረጃ 1 (stage 1) የ5ዓመት cancer specific survival ከ90%በላይ የሚደርስ ሲሆን በደረጃ 4(stage 4) 5አመት የመኖር ዕድል ደግሞ ከ5% በታች ነው።

የኩላሊት ካንሰር ህክምናዎች

1) ቀዶ ጥገና ህክምና(partial/radical/cytoreductive nephrectomy)፦ ለሁሉም የኩላሊት ካንሰር ደረጃዎች የሚደረግ ህክምና ነው(ወደሳንባ፣ አጥንት፣ ጉበትና አንጎል የተሰራጨን ካንሰር ጨምሮ) ።

2) የጨረር ህክምና፦ ወደ አጥንት(spine) እና አንጎል የተሰራጨውን ካንሰር ለማከም እንደ አማራጭ ህክምና ይወሰዳል።

3) Target and immunotherapy: በዋጋ ደረጃ ውድ ሲሆኑ በህይወት የመኖር ጊዜን እምብዛም አይጨምሩ

4) ኬሞ ቴራፒ(chemotherapy): የኩላሊት ካንሰር ሁሉንም ኬሞ ቴራፒዎች መቋቋም ስለሚችል እንደ አንድ የህክምና አማራጭ አይወሰድም።

የኩላሊት ካንሰር መጥፎ ትንቢያዎች(poor prognosis signs) ከሚያሳዩት ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው።

1) የወረደ የሰውነት ወቅታዊ አቋም(poor performance status)

2) ትልቅ የዕጢ መጠን(larger tumor size)

3) ከፍተኛ የካንሰር ደረጃ(higher tumor stage)

4) የተሰራጨ ካንሰር(distant metastasis)

5) መጥፎ ካንሰር አይነት (bad histology type like collecting duct and renal medullary ca) እና ሌሎችም።

መውጫ:- የኩላሊት ካንሰር ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገለት ሰው ከህክምና ክትትል መጥፋት የለበትም ምክንያቱም እስከ 2-4% ድረስ ድጋሜ የመከሰት ዕድል(recurrence) ሊኖር ስለሚችል።

የኩላሊትና ሽንት ቧንቧ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት(Urologist)

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *