#ቃር /Heartburn
• ቃር የምንለው ወይንም በህክምና አጠራሩ ሃርትበርን (Heartburn) በመባል የሚታወቀው የህመም አይነት ሲሆን አብዛኞችን የሚያጠቃ እና እጅግ የተለመደም ችግር ነው።
በደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት መሰማት በአብዛኛው ከምግብ በኃላ እና እንቅልፍ ስንተኛ የሚብስ ነው። ይህም የሚከሰተው የጨጓራ ውስጥ አሲድ ወደ ላይኛው የምግብ አስተላላፊ ቱቦ ሲገባ ነው።
✔ ለቃር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች?
• ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
• ሽንኩርት
• ሲትረስ ያላቸው ምግቦች
• ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች
• ጣፋጭ ምግቦች
• የአልኮል መጠጦችን መውሰድ
• ካፊን ያላቸውን መጠጦች መውሰድ
• ከጥጋብ በላይ መመገብ
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት
• ነፍሰጡርነት ናቸው።
ቃር በአብዛኛው አመጋገብን በማስተካከል እና ቀስቃሽ ሁኔታዎችን በማስወገድ የሚድን ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የደረት ማቃጠል፣ ውጋት፣መጨምደድ ስሜት እና ወደ ትከሻ የሚሰራጭ የህመም ስሜት ከትንፋሽ ማጠር ጋር ከተከሰተ በአፋጣኝ ሃኪም ማማከር ተገቢ ነው ምክንያቱም የድንገተኛ ልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ነው።
✔ ከዚህ በተጨማሪ
• በሳምንት ውስጥ ከሁለት ጊዜ በላይ የሚያቅርዎ ከሆነ
• ለመዋጥ የሚችገሩ ከሆነ
• ማቅለሽለሽና ማስመለስ ካልዎት
• የምግብ ፍላጎት በማጣት ወይንም ለመመገብ በመቸገር ምክንያት የሰውነት ክብደትዎ ከቀነሰ ሃኪምዎን ማማከር ይኖርብዎታል።
✔ ቃርን ለማስታገስ መደረግ ያለባቸው የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች
• የሰውነት ክብደትዎን ማስተካከል
• ቃርን የሚይያስነሱ ምግቦችን አለመመገብ
• የአልኮል መጠጦችን አለመውሰድ
• ሲጋራን አለማጤስ
• በመኝታ ጊዜ ጭንቅላትዎን ከፍ ባለ ትራስ ላይ ማሳረፍ ናቸው።
በጨጓራዎ ውስጥ የሚመነጨውን ከመጠን በላይ አሲድ(Hyperacidity) በቀላሉ በማስወገድ የቃር ችግሮን በነዚህ ምክሮች ያስወግዱ
ምግብን እንዲፈጭ የሚያደርግ ከጨጓራ የሚመነጭ ፈሳሽ ጋስትሪክ ጁስ ይባላል፡፡ የሚመነጨው አሲድ ማለትም ሐይድሮክሎሪክ አሲድ የበዛ እንደሆነ ሐይፐርአሲዲቲ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህ ነው በጨጓራ ላይ ቁስል የሚያስከትለው፡፡
ከመጠን በላይ አሲድ በጨጓራችን ውስጥ መከሰቱን የሚሳብቁ ምልክቶች
1. የሚያቃጥል የሕመም ስሜት ከጨጓራ ተነስቶ እስከ ደረት አልፎም ጉሮሮ ጋር የሚደርስ ቃር፡፡
2. መራራ አሲድ ወደ ጉሮሮ ወይም አፍ መድረስ፡፡
3. ሆድ መነፋት፡፡
4. ደም ወይም ጥቁር ነገር የቀላቀለ አይነምድር፡፡
5. ደም የተቀላቀለ ትውኪያ፡፡
6. ማግሳት፡፡
7. ምግብ ያለመፈጨት ችግር፡፡
8. ስቅታ፡፡
9. ማቅለሽለሽ፡፡
10. ያለምንም ምክንያት ክብደት መቀነስ፡፡
11. ደረቅ ወይም ፉጨት ያለው ሳል ወይም ዘላቂ የጉሮሮ ቁስል፡፡
12. የጆሮ ሕመም፡፡
ከመጠን በላይ አሲድ በጨጓራችን ውስጥ እንዲከሰት የሚያደርጉ አባባሽ ምክንያቶች
1. ብዙ ምግብ መመገብ ወይም ከተመገቡ በኃላ ወዲያውኑ ጋደም ማለት፡፡
2. ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት፡፡
3. ከባድ ምግብ ተመግበው በጀርባ መተኛት ወይም ወዲያውኑ አጎንብሰው ስራዎችን መስራት፡፡
4. በመኝታ ጊዜ ምግብ መመገብ፡፡
5. ውጥረት፡፡
6. አሲድ ያላቸው እንደ ብርቱካንና ሎሚ ፍራፍሬዎችን መመገብ፣ከዚህ በተጨማሪ ቲማቲም፣ቸኮሌት፣ነጭና ቀይ ሽንኩርት ወይም ቅመም ወይም ቅባት ያላቸውን ምግቦች መመገብ፡፡
7. የአልኮል፣የለስላሳና ካፊን ያለባቸው ቡናና ሻይ ምግብዎችን መመገብ፡፡
8. ሲጋራ ማጨስ ፡፡
9. ነፍሰጡር መሆን፡፡
10. አንዳንድ መድኃኒቶች እንደ አስፕሪን፣አይቢፕሮፍን፣አንዳንድ የጡንቻ ማፍታቻ ወይም የደም ግፊት ሕክምና መድኃኒቶችን መውሰድ፡፡
መፍትሔ
1. ቅመም የገባበትና ማጣፈጫ ያለበትን ወይም የተጠበሰ ምግብ አይብሉ፡፡
2. አልኮል መጠጦችን ያስወግዱ፡፡
3. ወተት፣ክሬም፣ቅቤ ይመገቡ፡፡
4. ሙዝ፣ማንጎ፣ሐብሐብና ቴምር የዘውትሩ፡፡
5. ምግብዎን ቶሎ ቶሎ አይመገቡ፡፡ በደንብ አኝከው ይዋጡ፡፡
6. በቀን ቢያንስ 8 ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ፡፡
7. ጣፋጭ ፣ቆምጣጣና ከፊኖ ዱቄት የተዘጋጁ ምግብዎችን አይመገቡ፡፡
8. ጠዋት ፍራፍሬ፣ምሳ የተቀቀለ አትክልት መብላት ያሻል ከምግብ በፊት ሁል ጊዜ አንድ ኩባያ አጥሚት ይጠጡ፡፡
9. በእግር መሄድ ያዘውትሩ ፡፤
10. በተቻለ መጠን ደስተኛ ይሁኑ፡፡
11. ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ፀረ- አሲድ መድኃኒት በመግዛት በመድኃኒት ባለሙያ ምክር ይውሰዱ፡፡
መልካም ልምምድ መልካም የጤና ጊዜ ይሁንልዎ!
እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!
እኛን በአካልም ሆነ በስልክ ማማከር ወይም ማግኘትከፈለጉ
በቀጣዩ ቴሌግራም ሊንክ ቅድሚያ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇
ማጠቃለያ
ቃር (የደረት ማቃጠል) Acidc Reflux Disease
• ይህ በሽታ በዘልማድ ልቤን አቃጠለኝ እያሉ የሚያወሩለት ነው።
• የሚፈጠረው በተፈጥሮ ሆድ ውስጥ ያለው አደገኛ አሲድ በትነት ወይም በጋዝ መልክ ወደ ጉሮሮ(የላይኛው የምግብ ትቦ) ሲወጣ ነው።
• ከምግብ በኋላ የታችኛው የደረት ክፍል ላይ የማቃጠል ስሜት ሲፈጥር ነው።
• በሳምንት ሁለትና ከዚያ በላይ ካጋጠመ የጤና ባለሙያ ማማከር ያስፈልጋል።
• አመጋገብን በማስተካከልና በመድሀኒት መታከም ይችላል።
• ምክናየቱ ብዙ ጊዜ ባይታወቅም እርግዝና፡ ዉፍረት፡ ማጤስ፡ አንዳንድ መድሀኒቶች፡ አነቃቂ መጠጦች፡ አልኮል፡ መጠኑ የጨመረ ጨው፡ ብዙ መብላት፡ ቸኮሌት፡ አሲድ መጠናቸው ከፍ ያለ ጭማቂዎችና የመሳሰሉት ያስነሱታል። ያባብሱታል።
• በጣም የተለመደና ብዙዎችን የሚረብሽ በሽታ በመሆኑ የጤና ባለሙያን በማማከር ከህመሙ መዳን ይችላሉ።
ጤናችን በጃችን ነው።
እባከዎ መረጃውን ለሌሎች በማድረስ ይተባበሩን!!!!