አለምን እያስጨነቀ ያለው የኒውክሌር አብዮት

ኒውክሌር የአለማችንን የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ ግንኙነቶች በሙሉ በአጭር ጊዜ የለወጠ ክስተት ነው። በኒውክሌር ጨለማ ያጠላባቸው ከተሞች ብርሀንን እንዲያገኙ እና ትላልቅ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ስራቸውን እንዲሰሩ ማድረግ ቢቻልም በኒውክሌር ምክኒያት ከተሞች ወድመዋል፣ ህይወትም ጠፍቷል። ግን ኒውክሌር ምንድን ነው? እንዴትስ ይህንን ያህል ተጽዕኖ በአለማችን ላይ ሊኖረው ቻለ?

ኒውክሌር ወይም የኒውክሌር ሀይል ማለት የኒውክሌር አጸገብሮት (reaction)ን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ሀይልን ማመንጨት ማለት ነው። የአንድን ኬሚካል አተም ውስጠኛ ክፍል የሆነውን ኒውክለስ ሁለት እና ከዚያ በላይ በመከፋፈል የኒውክሌር ሀይልን ለማመንጨት ይቻላል። ይህም ሂደት ኒውክሌር ፊዢን (Nuclear Fussion) ይባላል።

የኒውክሌር ማመንጫ ጣቢያዎች ከፍተኛ የሆነ ሙቀትን በመጠቀም እንደ ዩራኒየም ያሉ ኤለመንቶችን በመጠቀም ኒውክሌርን ያብላላሉ። ኒውክሌር እንደ ውሀ፣ ንፋስ እና የጸሀይ የኤሌክትሪክ ማመንጫዎች በቶሎ ወደ ሀይል ማመንጨት የሚገባ አይደለም። እጅግ ሰፊ ጊዜያትን ብሎም አመታትን ይወስዳል።

ኒውክሌር ከተብላላ በኋላ ያለውም ጭቃጭ በተቻለ መጠን እንደ እንስሳት እና እጸዋት ካሉ ህይወት ካላቸው ነገሮች በተቻለ መጠን ማራቅ ይገባል። በርግጥ ፈጣን ሪያክተር ያላቸው እንደ ሩሲያ እና ፈረንሳይ ያሉ ሀገራት የኒውክሌር ዥቃጭ በከባቢ አየር እና በብዝሀ ህይወት ላይ የሚያስከትለውን ችግር ለመቅረፍ ብዙ እየሰሩ ነው። ቢሆንም ግን

እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1938 ገደማ የአተምን ውስጣዊ ክፍሎች በጥልቀት ለማወቅ በሚደረጉ ጥናቶች መሀል የአተሞችን ውስጠኛ ክፍል የሆነውን ኒውክሊየስ መከፋፈል ከፍተኛ የሆነ ቼይን ሪያክሽን (chain reaction) እጅግ የላቀ ሀይልን ማመንጨት እንደሚችል ተመራማሪዎች ለመረዳት ችለዋል። ከዚህ ግኝት በኋላ ጥናቶች በሰፊው በተለያዩ ምሁራን ሲካሄዱ ነበር። በ1942 ዓ.ም የዩናይትድ ስቴትስ ተመራማሪዎች የመጀመሪያ የሆነውን የኒውክሊየር ማብላያ ገንብተው ስራ ላይ አውለዋል። በወቅቱ የተቀሰቀሰውን የሁለተኛው የአለም ጦርነት መነሻ በማድረግ ከኒውክሊየር የሚገኘውን ሀይል አቶሚክ ቦምብ ለማዘጋጀት ተጠቅመውበታል። በሀምሌ 1945 የመጀመሪያው የኒውክሊየር ሙከራም ከተደረገ ከአንድ ወር ጊዜ በሁላ ሂሮሽማ እና ናጋሳኪ በተባሉ የጃፓን ከተሞች ላይ አደጋ እንዲያደርስ ተደርጓል።

በመጀመሪያ ቦምቡ የተጣለው በሂሮሽማ ሲሆን የወቅቱ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሱዙኪ በዚህ አንደናገጥም አሁንም እንዋጋለን በማለታቸው ምክኒያት ከሶስተኛው ቀን በኋላ በናጋሳኪ ከተማ በድጋሚ የኒክሊየር ቦምብ ተጥሏል። እነዚህ አቶሚክ ቦምቦች በእነዚህ ከተሞች ላይ እንዲወድቁ የተደረገው ከተሞቹ ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ቁጥር ያላቸው እና የጃፓን ጦር ሀይል ዋና የሚባሉ ቢሮዎች የሚገኙበት በመሆኑ ነው። በቦምቦቹ ምክኒያትም ከ129,000 እስከ 226,000 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን ህይወት ተቀጥፏል። ከሁለቱ ትልልቅ አደጋዎች በኋላ ጃፓን ለተባበሩት ሀይሎች እጇን ሰጥታለች።

ይህ እጅግ አሳዛኝ ታሪክ ቢሆንም የኒውክሊየር ሀይልን ለመልካም አላማ ለማዋል በሚል እሳቤ በ1953 ዓ.ም የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት የነበሩት ድዋይት ኢሰንሀወር (Dwight Eisenhower) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ላይ አተሞችን ለሰላም (Atom’s for peace) በሚል ርዕስ ንግግር አድርገው ነበር።

ከዚያን ጊዜ ወዲህ የኒውክሌርን ሀይል ለኤሌክትሪክ ፣ ሰርጓጅ መርከቦችን ለማሽከርከር እና የስፔስ መኪኖችን ለማንቀሳቀስ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል። ከዚህ ባለፈም ምናልባት ወደፊት የአለም ጦርነት ቢነሳ ራሳቸውን ለመከላከል በሚል ሰበብ ኒውክሊየርን የሚያብላሉ ሀገራት አሉ። እነዚህም ሀገራት አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ፓኪስታን እና ሰሜን ኮርያ ሲሆኑ አብዛኛው ሀገራት እና ባለሙያዎች እስራኤልም የኒውክሊየር ሀይል እንደምታመነጭ ቢናገሩም እርሷ ግን እስካሁን ድረስ አላመነችም።

ኒውክሊየር በትንሽ መጠን ትልቅ የሆነ ሀይልን ማመንጨት የሚችል መሆኑ እና በተለይም ከባባድ አጥፊ የሆኑ መሳሪያዎችን ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ ሀገራት ታላቅነትን ለማግኘት ሲሉ ሰፊ ትኩረት ከሰጡት ሰነባብተዋል። ይህም እነሱ ኖሯቸው ሌላው እንዳይኖረው እስከ መታገል ድረስ አድርሷቸዋል። ከዚህም የተነሳ በሀገራት መሀል ቁርሾ እየሰፋ መጥቷል። የኒውክሌር ባለቤት መሆን በሌሎች ላይ ሀይልን ለመጎናጸፍ እና ተፈሪነትን ለማግኘት እንደ ቁልፍ ሆኗል።

በርግት ሁሉም ሀገራት እንደልብ ማግኘት የሚችሉት ነገር ይሁን ተብሎ ቢተው እና በማንም እጅ መግባት የሚችል ከሆነ ለእርስ በርስ ግጭቶች እና ለመጠፋፋት እንደሚውል ግልጽ ነው። በተወሰኑ ሀገራት እጅ ብቻ ይግባ ቢባል ደግሞ እነዚያ ሀገራት ይህንን እንደ እድል በመጠቀም ሌሎች ላይ ለመሰልጠን እና ለማጥፋት ሊያውሉት ይችላሉ። ይህ ሁሉ ስጋት እና ውዝግብ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ለረዥም ጊዜያት እስካሁን ድረስ ሲያወዛግብ ቆይቷል። ወደፊትም መቀጠሉ አይቀርም።

የኒውክሊየር ባለቤት ማን ይሁን ከሚለው ጥያቄ ባለፈ የኒውክሊየር ዝቃጭ ትልቅ አወዛጋቢ ጉዳይ ነው። ከኒውክሊየር ሀይልን ለማመንጨት በሚደረገው የኬሚካዊ አጸገብሮት ከፍተኛ የሆነ የራዲየሽን ኢነርጂ ስለሚፈጠር ከዚህ የሚወጡ ተረፈ ምርቶች ቀላል የማይባል ጉዳትን ያስከትላሉ። ዝቃጮች ወደ አካባቢ ከመቀላቀላቸው በፊት ቢያንስ ለሺህ አመታት ያህል ህይወት ካላቸው ነገሮች ራቅ ሊደረጉ ይገባል። ከዚህ በተጨማሪ ከኒውክሊየር ሀይል የሚወጣው ጨረር ለአለም ሙቀት መጨመር እጅግ ትልቅ አስተዋጽኦ ከመሆኑ ባለፈ የጨረሩ ሀይል በአካባቢ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ቀላል የሚባል አይደለም።

ኒውክሊየር በአንድ በኩል ትልቅ ስጋትን ይዞ ቢመጣም ለመልካም አላማ እስከዋለ ድረስ የሀይል አቅርቦት ጥያቄን ለመፍታት ትልቅ አቅም ያለው ነገር ነው። ከማብላላቱ ጀምሮ ሀይል እስከማመንጨት እንዲሁም ዝቃጩን የማስወገዱ ሁኔታ ላይ እጅግ ከፍተኛ የሆነ በሀላፊነት ስሜት እና ጥንቃቄ በተሞላ መንገድ መስራቱ ምንም አማራጭ የሌለው ወሳኝ ጉዳይ ነው። ከዚህ በተጨማሪም የኒውክሊየርን ሀይል ለጦር መሳሪያ ከማዋል ይልቅ ብርሀንን ላልደረሳቸው የአለም ክፍሎች ለማድረስ፣ የአለምን የምግብ ጥያቄ ለመፍታት እና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ፋብሪካዎችን ለማስፋፋት ፣ የጠፈር ምርምሮችን ለማቀላጠፍ ተግባር ላይ ቢውል ለሰው ልጆች ትልቅ የሆነን ጥቅም ይሰጣል።

በዚህ ቪዲዮ በትንሹም ቢሆን ስለ ኒውክሊየር ምንነት እና ስላለው መልካም እንዲሁም ክፉ የሆኑ ገጽታዎች ዳሰሳ አድርገናል። ሀሳብ እና አስተያየታችሁን በኮሜንት መስጫው ስር አስቀምጡልን። ስለተከታተላችሁን እናመሰግናለን።

22 thoughts on “አለምን እያስጨነቀ ያለው የኒውክሌር አብዮት”

  1. Xoilac TV trang trực tiếp bóng đá hôm nay. XoilacTV xem bóng đá Ngoại Hạng Anh, Champions League, Europa League, La Liga. Xôi Lạc TV không quảng cáo, sắc nét, có BLV tiếng Việt miễn phí.

  2. I would like to thnkx for the efforts you have put in writing this blog. I am hoping the same high-grade blog post from you in the upcoming as well. In fact your creative writing abilities has inspired me to get my own blog now. Really the blogging is spreading its wings quickly. Your write up is a good example of it.

  3. Hi, just required you to know I he added your site to my Google bookmarks due to your layout. But seriously, I believe your internet site has 1 in the freshest theme I??ve came across. It extremely helps make reading your blog significantly easier.

  4. Superb website you have here but I was curious if you knew of any user discussion forums that cover the same topics talked about in this article? I’d really like to be a part of community where I can get opinions from other knowledgeable individuals that share the same interest. If you have any recommendations, please let me know. Thanks a lot!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *